አርብ ረፋድ በበርካታ ጋዜጦች ላይ የወጡ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች!

1
0
SHARE

ማንቸስተር ሲቲዎች የሞናኮውን ተከላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ ለማስፈረም ሲሉ የተከላካዮች የዝውውር ሪከርድን ለመስበር ዝግጁ ናቸው፡፡ሲቲ ከዚህ ቀደም ለቶተንሃሙ ተከላካይ ካይሊ ወከር £50m አውጥቷል፡፡

 
ጁቬንቱስ የሊቨርፑሉን አማካይ ኤምሪ ቻን በማስፈረም የአማካይ ክፍሉን ማጠናከር ይፈልጋል፡፡የቻን ኮንትራት በሲዝኑ መጨረሻ ላይ ሲጠናቀቅ ጁቬንቱስ ተጨዋቹን በ€25m እንደሚያስፈርሙት ተስፋ አድርገዋል፡፡
 

ቶተንሃም የሌስተር ሲቲውን ሲቲውን የጨዋታ አቀጣጣይ ሪያድ ማህሬዝ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፡፡ተጨዋቹ ከኪንግ ፓወር ስታዲየም ለመልቀቅ £50m ተለጥፎበታል፡፡
 

ዎልፍስበርግ የማንቸስተር ዩናይትዱን አጥቂ አንቶኒ ማርሻል በቋሚ ዝውውር ለማስፈረም ጥዬቄ አቅርቧል፡፡ክለቦች ፈረንሳዊውን አጥቂ የማስፈረም ዕድላቸው የተገደበ ነው፡፡
 

ዲያጎ ኮስታ የአትሌቲኮ ማድሪድ የዝውውር እገዳ እስኪነሳለት ድረስ በኤሲ ሚላን በውሰት የመጫወት ዕድል አለው፡፡አጥቂው እስከ በጋ ድረስ የስፔኑን ክለብ ለመቀላቀል ስለማይችል የሴሪኣው ክለብ እስከ ጥር የዝውውር መስኮት በውሰት ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው፡፡
 
ማንቸስተር ዩናይትዶች ኤሲ ሚላንን በመርታት የባየር ሙኒኩን አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝ ለማስፈረም እየተመለከቱ ነው፡፡ጆዜ ሞሪንሆ ኤሪክ ዳየርን ከቶተንሃም ማስፈረም ካልቻሉ ሳንቼዝ ላይ ያተኩራሉ፡፡ባየር ሙኒክ አማካዩን በ£40m ለመሸጥ ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
 

አርሰናል ለካሉም ቻምበርስ የቀረበለትን የ£16m ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡ክሪስታል ፓላሶች ተከላካዩን የማስፈረም ፍላጎት ቢያሳዩም ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረቡት ጥያቄ በመድፈኞቹ ውድቅ ተደርጓል፡፡አርሰናል ተጨዋቹን ከ£20m መሸጥ አይፈልግም፡፡
 

ባርሴሎና የሊቨርፑሉን አማካይ ፊሊፔ ኮቲንሆ ለማስፈረም £72m አቅርቧል፡፡ነገር ግን ቀዮቹ ጥያቄውን ውድቅ ያደርጉታል፡፡
 

አርሰናሎች ሜሱት ኦዚል አዲስ ኮንትራት እንደሚፈርም ያላቸው መተማመን ከፍ ብሏል፡፡
 

ማንቸስተር ዩናይትዶች ከሞናኮው አማካይ ፋቢንሆ ጋር ለመስማማት በመቸገራቸው የፒኤስጂውን ቀኝ መስመር ሰርጂ ኦሪዬር በ£28m ለማስፈረም እየተመለከቱ ነው፡፡
 

የፒኤስጂው አለቃ ዩናይ ኤምሪ አይቮሪ ኮስታዊው ኢንተርናሽናል ሰርጂ ኦሪዬር በክረምቱ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ አረጋግጠዋል፡፡(L’Equipe Via Metro)
 

አርሰናል እና ቶተንሃም የማንቸስተር ሲቲውን የ17 አመት ክንፍ ጃደን ሳንቾ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፡፡
 

የቼልሲው አማካይ ቲሞ ባካዮኮ አዲሱን ፈራሚ አልቫሮ ሞራታ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ እንኳን ደህና መጣህ ብሎታል…
 

የስቶክ ሲቲው አጥቂ ማርኮ አርናቶቪች ወደ ዌስትሃም ለመዛወር ነገ የሜዲካል ምርመራውን ያደርጋል፡፡በክለቡ አዲስ የአምስት-አመት ኮንትራት ሲፈራረም ለዝውውሩ £25m ወጪ ይደረግበታል፡፡
 

ዌስትሃሞች የባየር ሊቨርኩሰኑን አጥቂ ጃቪየር ሄርናንዴዝ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል፡፡የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ የሜዲካል ምርመራውን ለማድረግ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ለንደን ይበራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here