በወላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

1
0
SHARE

በወላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለምዶ መርካቶ እየተባለ በሚጠራ የገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለምዶ መርካቶ እየተባለ በሚጠራ የገበያ ስፍራ ላይ ትናንት ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የወላይታ ሶደ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር አሸናፊ አዲሱ የአደጋዉ ጥሪ በስፍራው በጥበቃ ሥራ ላይ በነበሩ ግለሰቦች በኩል ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ለፖሊስ መድረሱን ገልጸዋል።

ጥሪዉ ከደረሰ በኋላ ሙሉ የፖሊስ አባላትና ድንገተኛ የእሳትና አደጋ መከላከል ቡድን ከሕብረተሰቡ ጋር ባደረገው ርብርብ እሳቱ የከፋ አደጋ ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ሊዉል መቻሉን ተናግረዋል።

በተከሰተው የእሳት አደጋ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 34 ሱቆች ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም 12 ሱቆች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ምንጭ ፡FBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here