የአርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስራት የሚፈፀምበት ቀን ተቆረጠ….

1
0
SHARE

የአርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስራት የሚፈፀምበት ቀን ተቆረጠ….

በትናትናው እለት ከዚህ አለም በሞት የተለዩን የዋናይ፤ሙዚቀኛ፤የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች አቶ ተስፋዬ ሳህሉ

ብዙሃኑ ከሚያውቅላቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ አዘጋጅነት ለረጅም አመታት በብዙሃኑ ልብ የማይጠፋ አስተማሪ ተረቶቻቸው ይታወቃሉ ።

አባባ ተስፋዬ ተረት አውሪ ናቸው>> ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ትልቅ ስህተት ነው… አባባ ተስፋዬ – ታሪክ ዘካሪ፥ እውነትን መስካሪ፥ ትውልድ የሚፈስበትን ቦይ ቀያሽ ናቸው”
ለየትኛውም ሃይማኖት ሳይጎረብጡ ከእምነት ተቋማት መምህራን ባልተናነሰ መልኩ በትውልድ ጆሮ የተደመጡ፥ በሕዝብ ህሊና የተከበሩ፥ እንኳን በልጆች በወላጆችም ዘንድ ውዳሴ የተቸራቸው፥ ስነምግባርን በፍቅር ተርከው፥ በትህትና አስተምረው፥ በአባትነት ቃል የገሰጹ፥ ፈጣሪን የሚፈሩ፥ ሰውን የሚያከብሩ፥ ለማህበረሰቡ እሴት ተገዢ የሆኑ ህፃናትን፥ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በቀና ንግግር ገርተው የዜግነት ድርሻቸውን በክብር የተወጡ ናቸው

የአርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ፤ (አባባ ተስፋዬ) ሥርዓተ ቀበር ነገ፣ ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2009ዓ.ም.

በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል
***
ምንጭ ፤ ጌጡ ተመስገን የፌስ ቡክ ገፅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here